Amharic
መብቶችዎን ይወቁ፣
የመጨረሻ ኣቅርቦት (offer) ድምፆች
British Columbia and Ontario
Select your language below
Know your Rights!
“የመጨረሻው ኣቅርቦት (offer) ድምፅ” ምንድን ነው እና ለምን ስለሱ ማወቅ አለብን?
- በኦንታሪዮ/ብሪቲሽ ኮሎምቢያ፣ የስራ ማቆም አድማው ከመጀመሩ በፊት፣ በቀጣሪው “የመጨረሻ ኣቅርቦት (offer) ላይ በማህበር አባላት ድምፅ እንዲሰጥ ቀጣሪ ለክልሉ መንግስት መጠየቅ ይችላል።
- ኣንድ ቀጣሪ “የመጨረሻ ኣቅርቦት (offer) ድምፅ” ዘዴን ለመጠቀም ሲጠይቅ፣ ሠራተኞች በቂ ያልሆነ ውል እንዲቀበሉ ጫና ለማድረግ ነው። ይኸም ድንጋጤ ለመፍጠር እና ሠራተኞች ለዓመታት በመጥፎ ውል በኣጣብቂኝ አደጋ ውስጥ እንዲገቡ ታስቦ ነው።
- እንደ የሠራተኛ ማኅበር የዋጋ ተደራዳሪ ኮሚቴ የእኛ ሥራ ከአሠሪው ጋር ለሠራተኞች የሚቻለውን ያህል የበለጠ ኣቅርቦት (offer) ለመደራደር ነው።
- ኣንድ ቀጣሪ “ለመጨረሻ ኣቅርቦት (offer) ድምፅ” ዘዴን ሲጠቀም ሆን ብለው ኮሚቴዎን በማለፍ/በመዝለል ፍርሃት እና ግራ መጋባት ለመፍጠር ሠራተኞችን ለመከፋፈል እየሞከሩ ነው።
ቀጣሪያችን ለሠራተኞች “የመጨረሻ ኣቅርቦት (offer) ድምፅ” የሚልኩ ከሆኑ ምን ይሆናል?
- ኣንድ አሠሪ ስለ ኣቅርቦት (offer) ያቀረቡት ሓሳብ መረጃ የያዘ ማስታወቂያ ለሠራተኞች ይልካሉ። ለአዲስ ውል ፍትሃዊ እና ምክንያታዊ ውል አድርገው ያዋቅራሉ።
- የአውራጃው የሠራተኛ ሚኒስቴር መላውን የሠራተኞች ቡድን በኦንላይን/ኢንትርነት ድምፅ (vote) እና ድምፅ መስጫ (ballot) በአሠሪው ኣቅርቦት (offer) ላይ ድምፅ እንዲሰጡ የሚጠይቅ በኢመይል ያሳውቃል።
- የአለቃውን የመጨረሻ ኣቅርቦት (offer) በጭራሽ መቀበል የለብዎትም – አይ በማለት ድምፅ መስጠት ይችላሉ!
- አብላጫ ድምፅ ኣይ ማለት የእርስዎ ማህበር ተደራዳሪ ኮሚቴ የተሻለ ውል ለማሸነፍ ወደ ድርድር መመለስ ይችላል ማለት ነው።
- ከዚያ፣ ዝግጁ ከሆንን፣ የሥራ ማቆም ኣድማ ለማድረግ እንችላለን!